የሰንበት ትምህርት ቤት
እግዚአብሔር አምላክ የሰውንልጅ በአርያውና በአምሳሉከፈጠረ በኋላ ሰው ከፈጣሪውጋር በጥብቅ እንዲናገናኝ ልዩልዩ የአገልግሎት መንገዶችንአዘጋጀ። እያንዳንዱ በተሰጠውመክሊት ያተርፍና በጸጋውያገለግል ዘንድ በመጀመርያዕድሜው በፈቀደለት ሁሉመማርና ማገልገልይኖርበታል። እግዚአብሔርአምላክ መመለክ በአለበትአግባብ ለማምለክ እምነትያስፈልጋል፤ ከእምነትእንዳንወጣ ደግሞስለምናምነው ነገር በቂዕውቀት ሊኖረን ይገባል፤እምነትን፣ ተስፋና ፍቅርን ሰንቆእስከመጨረሻ ድረስ ለመጽናትመንፈሳዊ ዕውቀት መሠረታዊነው።
“ህዝቤ ዕውቀት በማጣትጠፍቷል” (ሆሴ 4፥6)የተባለው በእኛ ላይእንዳይፈጸም ዕድሜያችንበሚፈቅድልን ሁሉ ሃይማኖታዊዕውቀትን እንድንማር ቤተክርስቲያን በቅዱሳን ጸሎትበእግዚአብሔር መልካምፍቃድ ሰንበት ት/ቤትንአቋቋመች። ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ልጆቿ ጽድቅንይማሩ ዘንድ በሰንበት ት/ቤትአሰባስባ ቃለ እግዚአብሔርንአውቀው፣ ባሕርየእግዚአብሔርን ተረድተውእንዲያመልኩ፣ ሕጉንጠብቀው፣ በሃይማኖት፣በምግባርና በትሩፋት ፀንተውአምላካቸውን መስለውእንዲኖሩ የእርሱ የሆነችውንመንግስተ እግዚአብሔርንእንዲወርሱ በብሉይ ከአምላኳየተቀበለችውን ሕግጋተእግዚአብሔርን አስተምራበሐዲስ ኪዳንም በ40 እናበ80 ቀን እያጠመቀችለምዕመናን እንደ እድሜያቸውእና እንደ አዕምዕሮብስለታቸው ቃለእግዚአብሔርን ደከመኝ ሰለቸኝሳትል ታስተላልፋለች።በስብከት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴ፣በስዓታት፣ በማሕሌት የቅኔውንምሥጢር በትርጓሜእያስተማረች ምዕመናንንበእምነት አንፃ ለመንግስተሰማያት እያዘጋጀች ዛሬ ላይደርሳለች።
ከስሙ እንደምንረዳው ሰንበትትምህርት ቤት ማለት የጾታልዩነት ሳይደረግ የቤተክርስቲያን ተተኪ ትውልድወይም መንፈሳዊ ወጣቶችበዕለተ ሰንበት፣ በዓበይትበዓላትና አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉበአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንእየተገኙ የቤተ ክርስቲያንንዶግማ፣ቅኖና፣ሥርዓትናትውፊት የሚማሩበት እናበእምነት፣በምግባርናበሃይማኖት ጸንተው ይኖሩዘንድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውንየሚያጠነክሩበት ትምህርትቤት ነው:: መንፈሳዊ ወጣቶችየሚባሉት የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊትበዕድሜ ክልላቸው የሚማሩየቤተ ክርስቲያን አባላት ናቸው(ቃለ ዓዋዲ ፲፱፻፺፩)።
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበት ት/ቤት ተብሎ የተፃፈ ቀጥተኛየሆነ ስም ባይገኝም ዛሬ ላይበሰንበት ት/ቤት የሚተገበረውመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትምልጆችን በቤተ እግዚአብሔርማስተማር በብሉይ ኪዳንዘመንም ይፈጸም እንደነበርመጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል።የሰንበት ት/ቤት ፅንሰ ሀሳብምከዚያ የመነጨ ነው። “እነዚህንቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁአኑሩ እነርሱንም ለምልክትበእጃችሁ ላይ እሠሯቸውበዐይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁን ልጆቻችሁንምአስተምሯቸው በቤትህምስትቀመጥ በመንገድምስትሄድ ስትተኛም ስትነሣምአጫውቱአቸው” (ዘዳ11÷18-21 )በማለትእስራኤላውያን ልጆቻቸውንሕግጋተ እግዚአብሔርእንዲያስተምሯቸው ታዘዋል፡፡እነርሱም ይህን አምላካዊ ቃልተግባራዊ ለማድረግልጆቻቸውን ወደ ቤተእግዚአብሔር እየላኩ እናበቤታቸው ውስጥም ተግተውያስተምሩ ነበር።
በሐዲስ ኪዳንምመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስበመዋዕለ ሥጋዌ ልዩ ትኩረትከሰጣቸው ቁም ነገሮችመካከል ሕፃናት ወደ ቤተክርስቲያን ይመጡ ዘንድ ነበር።ልበ ንጹሐንን በሕጻናት መስሎያስተማረበት አንቀጽምበመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፎይገኛል። ይህም በዘመናችንላለችው ቤተ ክርስቲያንየሕፃናት፣ የወጣቶች እናየጎልማሶች ማስተማሪያለሆነችው ሰንበት ትምህርትቤት መነሻ የሆነ እናመሠረቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊመሆኑን ያረጋግጥልናል (ማቴ18፥3፣ 21፥16፣ ማር 9፥37)፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤትአመሠራረት በኢትዮጵያስንመለከት ዘመናዊ ትምህርትቤት እየተስፋፋ ሲመጣ ወጣቱትውልድ ከአምልኮተእግዚአብሔር እንዳይለይ፤በተለይ ለዘመናዊ ትምህርትአስተማሪነት በመጡእራሳቸውን ”ኢየሱሳውያን”ብለው በሚጠሩ የውጭመምህራን ከመጡበትዓለማዊ ትምህርት ባሻገርየኑፋቄ ትምህርትማሰራጨታቸው፣ በተቃራኒውደግሞ ወደ አብነት ትምህርትቤት የሚሄደው ወጣት ቁጥርበመቀነሱ ምክንያት በ20ኛውክፍለ ዘመን ወጣቱን ለመያዝመንፈሳዊ መርሐ ግብሮችናየማኅበራት እንቅስቃሴዎችተጀመሩ። እነዚህ የተጀመሩመርሐ ግብሮችና ማኅበራትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያንአስተምህሮዎቿ ሳይበረዙለትውልድ እንዲተላለፉ በተለይበሕጻናት እና በወጣቶች ላይትኩረት ሰጥው እንዲሠሩትልቁን ድርሻ ወስደዋል።
በዚህም መሠረት ሰንበትትምህርት ቤት በማቋቋምትውልድን በኦርቶዶክሳዊሃይማኖት የማነጽ፣ ዶግማን፣ቀኖናን እና ትውፊትንማስተማር ተጀመረ። በ1960ዓ.ም ይህን የሰንበት ትምህርትቤቶች እንቅስቃሴለማስተባበር እና ለማጠናከርይቻል ዘንድ በጠቅላይ ቤተክህነት በስብከተ ወንጌልናማስታወቂያ መምሪያ ሥርማእከላዊ ጽ/ቤት በዋናነትተቋቁሞ ስያሜውም የሰንበትት/ቤት መምህራን ጽሕፈት ቤትተብሎ ተሰይሟል፡፡ ይህአካሄድ እያደገ ሲመጣበ1965 ዓ.ም ራሱን ችሎ ወደወጣቶች ጉዳይ መምሪያነትእንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ላይየሰንበት ትምህርት ቤትማደራጃ መምርያ የሚልሰንበት ትምህርት ቤቶችንየሚያደራጅና የሚመራበተቋም ደረጃ ትልቅ መምርያተቋቁሞ አገልግሎቱንእየፈጸመ ይገኛል።
የሰንበት ት/ቤት ጥቅሙናአስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑበተግባር በመረጋገጡበ1970 ዓ.ም “ሰንበት ት/ቤት” በሚል ስያሜ ሕጋዊ ሆኖእንዲቀጥል እና በሁሉምአብያተ ክርስቲያናት ውስጥሰንበት ት/ቤቶች እንዲቋቋሙየተቋቋሙትም እንዲጠናከሩተሻሽሎ በወጣው ቃለ ዓዋዲእንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡ የሰ/ት/ቤት አገልግሎትን የበለጠለማጠናከር ሰንበት ት/ቤቶችየሚመሩበትን መተዳደሪያደንብ አጽድቆ ሥራ ላይእንዲውል ያደረገ ሲሆን አሁንአስካለንበት ዘመን ድረስሰንበት ት/ቤቶች ይህንመመሪያ ከዋናው ቃለ ዐዋዲጋር በማስተባበርእየተመሩበትና ዘርፈ ብዙአገልግሎቶችን እየፈፀሙይገኛሉ፡፡
ይህን ወጣቱን ትውልድበዘመናዊነት ተፅዕኖ ውስጥወድቆ ከመንፈሳዊ ሕይወትእንዳይወጣ ልዩ ክትትልበማድረጉ ረገድ ኢትዮጵያ ብቻሳትሆን እኅት አብያተክርስቲያናትም ሰንበትትምህርት ቤትን አቋቁመውአገልግሎት መስጠት ከጀመሩብዙ ዓመታትን አስቆጥረዋል።በተለይ ግብፅና ሕንድበተደራጀ መልኩ እየሠሩበትይገኛሉ።
የሰንበት ትምህርት ቤትየተቋቋመበት ዋና ዓላማ
የሰንበት ትምህርት ቤትዓላማ፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንዶግማ፣ ቅኖና፣ እምነትናሥርዓት ተጠብቆሳይበረዝ ሳይከለስከትውልድ ወደ ትውልድእንዲተላለፍ ማድረግ
ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነምእመን የሃይማኖቱንሥርዓት በውልእንዲያውቅና እንዲረዳማድረግ
ወጣቶች የቤተክርስቲያንን ሕግና ሥርዓትተምረው ለሀገርና ለወገንጠቃሚ፣ መልካምና በሥነምግባር የታነፁ ዜጎችእንዲሆኑ ማድረግ
በጉብዝናህ ወራትፈጣሪህን አስብ (መክ.፲፪፡፩) የሚለውን የአምላክተእዛዝ ወጣቶችእንዲፈጽሙ ማስቻል
እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትንአበይት ዓላማዎች ከግብለማድረስ ጠንካራ ሰንበትትምህርት ቤት ያስፈልጋል።ወጣቶችን በሰንበት ትምህርትቤት ለማሳደግ ከጠቅላይ ቤተክህነት እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ሁሉም ባለ ድርሻአካላት የበኩላቸውን መወጣትበእጅጉ አስፈላጊ ነው።አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስለቅዱስ ጴጥሮስ ከሰጠውመመርያና ትዕዛዝ መካከልሕፃናትንና ወጣቶችንበሃይማኖት እያስተማረለመንግስተ ሰማያት ማብቃት